Ethiopian Energy^Power Business Portal,eepBp

የመንግስትን የግዥና የፋይናንስ ስርዓት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል አሰራር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደረገ። ኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዢ ሥርዓት (e-GP) እና የአፈፃፀም ስትራቴጂ አሰራሩ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ከመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

የመንግስትን የግዥና የፋይናንስ ስርዓት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል አሰራር በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ይፋ ይፋ የተደረገው። አሰራሩን በሌሎች የመንግስት መስርያ ቤቶች ለማስፋፋት የሚያስችል ስምምነትም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ተፈራመዋል። ስምምነቱን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩርያ እና የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ማርታ ሌዊጂ ፈርመውታል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩርያ በዚሁ ወቅት፦ የግዢና የፋይናንስ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የበለጸገው አሰራር በቀድሞ መገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለአንድ ዓመት ያህል የተሞከረ መሆኑንም ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Source: Fana Broadcasting

            thereporterethiopia/Agency unveils digital procurement strategy, roadmap

0
0
0
s2smodern

Add comment


Security code
Refresh