ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስማርት ሜትር መሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማከናወን የሚያስችለውን የውል ስምምነት ዛሬ ታህሳስ 06 ቀን 2013 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት ተፈራርሟል፡፡
የውል ስምምነቱ የተፈረመው ኑሪ ቴሌኮም በተሰኘ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መካከል ሲሆን፤ ወሉን የተፈራረሙት ደግሞ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅምንት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመቀ ሮቢ እንዲሁም የኑሪ ቴሌኮም ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኪን ያንግሂዊ ናቸው፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምሮ ከሁሉት ተቋማት የሚመለከታቸው የሥየስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በፌርማ ስነስርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ዛሬ የተፈረመው የስማርት ሜትር የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የውል ስምምነት ለተቋሙ የገቢ ስብሰባ አስፈላጊና ወሳኝ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ትግበራ ሊገባ ይገባል ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚ አክለውም ተቋሙ በፓይለት ደረጃ የሚተገብረው ይህ ፕሮጀክት ዘመናዊ አሰራር ለመዘርጋትና ቀልጣፋ አገልገሎት ለመስጠት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ ኩባንያ ተመርጦ ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል፡፡
የኑሪ ቴሌኮም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኪን ያንግ ሂዊ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር አብረው ለመስራት ዕድሉ ስለተሳጣቸው አመስግነው፤ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
የስማርት ሜትር የመሰረተ ልማት ዝርጋታው የውል ስምምነት አጠቃላይ ወጪ 12 ሚሊዮን 546 ሺህ 54 የአሜሪካ ዶላር እና 9 ሚሊዮን 640 ሺህ 450 ብር ነው፡፡
የስማርት ሜትር የመሰረተ ልማት ዝርጋታው የውል ስምምነት 2 ሚሊዮን ስማርት ቆጣሪዎችን ማስተናገድ የሚችል የሲስተም ዝርጋታ ሲኖረው፤ በፓይለት ደረጃ ደግሞ 50 ሺህ ቆጣሪዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚተከልበት ይሆናል፡፡ ከዚህ ውስጥ 5 ሺህ ያህሉ በኑሪ ቴሌኮም እንዲሁም ቀሪው 45 ሺህ ቆጣሪዎች ደግሞ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይከናወናል፡፡
ፕሮጀክቱ የዲዛይን፣ የአቅርቦት፣ የኢንስታሌሽን እና የኮሚሽኒንግ ስራ የሚያካትት ነው፡፡ ተግባራዊ የሚደረገው ስማርት ሜትር ፓይለት ፕሮጀክት ለከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ሲሆን፤ የሃይል ብክነትን ለማስቀረትና የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡
You are not authorised to post comments.
Comments will undergo moderation before they get published.