Ethiopian Energy^Power Business Portal,eepBp

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 

በኦሞ ወንዝ ላይ የተጀመረው የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ግንባታው መስተጓጎሉ ተሰማ፡፡ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ቀጥሎ በኢትዮጵያ ትልቁ የሆነው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ከጅምሩ የፋይናንስ ግኝቱ ችግር እንዳለበት ሲገለጽ የቆየ ቢሆንም፣ የፋይናንስ እጥረቱ ሥር እየሰደደ መጥቶ ሠራተኞችን መቀነስ ተጀምሯል፡፡ ፕሮጀክቱ በግንቦት 2008 ዓ.ም. ሲጀመር ዋነኛ ሥራ ተቋራጩ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ነበረ፡፡ ሳሊኒ ያስገኘው ብድር ሙሉ በሙሉ ከፍተኛ ወለድ የሚከፈልበት (ኮሜርሻል ብድር) በመሆኑ፣ የተወሰነው ክፍል አነስተኛ ወለድ በሚያስከፍል ብድር (ኮንሴሽናል ብድር) እንዲከናወን ለቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ዳንግ ፋንግ ኢንተርናሽናል እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር፡፡ አሁን ግን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ብድሩ በኮሜርሻል ተጠቃሎ ሥራው ሙሉ በሙሉ በሳሊኒ እንዲካሄድ ፍላጎት አሳይቷል፡፡

የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በደቡብ ክልላዊ መንግሥት በኮንታ ልዩ ወረዳ፣ በዳውሮና በጎፋ ዞኖች መካከል ይገኛል፡፡ የኮንታ ልዩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ልዩ ወረዳው ከኮይሻ ፕሮጀክት ጋር አብሮ የሚሠራው በፀጥታና በሠራተኛ ቅጥር ነው፡፡

‹‹የአካባቢው ሰላምና ፀጥታ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፣ ለፕሮጀክቱ የተቀጠሩት የአካባቢው ሠራተኞች እየተቀነሱ ነው፡፡ ምክንያቱን በግልጽ ባናውቅም በበጀት ዕጥረት እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሠራተኛ ቅነሳው ኋላ ላይ ማኅበራዊ ቀውስ ሊፈጥር ስለሚችል፣ በዚሁ ከቀጠለ ለክልሉ መንግሥት ሪፖርት እናደርጋለን፤›› በማለት ፕሮጀክቱ ያለበትን ደረጃ አቶ ፋንታሁን ገልጸዋል፡፡

የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግንባታ ለማካሄድ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተረከበው የጣሊያኑ ኩባንያ ሳሊኒ ኢምፕሪጂሎ ኤስፒኤ ሲሆን፣ ሥራውን በአጠቃላይ በዋና ተቋራጭነት (ኢንጂነሪንግ ፕሮኪዩርመንት ኮንትራት) ለማካሄድ ውል ተገብቶ ነበር፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 2,200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ሥራው በአጠቃላይ 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ይፈልጋል፡፡

ነገር ግን ከመነሻው ፕሮጀክቱ ያስፈልገዋል በተባለው 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ግኝት ላይ አለመግባበት ተፈጥሮ የቆየ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ከግንቦት 2008 ዓ.ም. ወዲህም በሌላ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡

ያለመግባባቱ መንስዔ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የብድር ጫና ያለባት አገር ሆና እያለ፣ ይህንን 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ከፍተኛ የባንክ ወለድ በሚጠይቀው የኮሜርሻል ብድር ሥርዓት ለማካሄድ ውል መግባቷ ነው፡፡

በኮሜርሻል ብድር አሠራር በሳሊኒ አማካይነት ከውጭ ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ እስካሁን 328.9 ሚሊዮን ዩሮ፣ እንዲሁም 9.4 ቢሊዮን ብር ከተከፈለ በኋላ፣ ቀጣዩ ገንዘብ እንዲለቀቅ ተጨማሪ ስምምነት የሚጠይቅ በመሆኑ የፋይናንስ አቅርቦቱ ተስተጓጉሏል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ኅዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ለገንዘብ ሚኒቴስር በጻፉት ደብዳቤ፣ በኮሜርሻል ብድር ሊከናወኑ ታስበው ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች ገንዘብ እንዲለቀቅ ጠይቀዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹በአሁኑ ጊዜ ብዛት ያላቸው ፕሮጀክቶች እየሠራን ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በኮሜርሻል ብድር ሊሠሩ ታስበው የተጀመሩ በመሆናቸውና አሁን በተሰጠው አቅጣጫ ማስቀጠል ባለመቻሉ፣ ሥራውን በተገቢው ፍጥነት ለመፈጸም የሚያስችል ሰፊ የገንዘብ እጥረት አጋጥሟል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ለሥራው ውል የተገባው 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ነው፡፡ በውጭ ምንዛሪ 1.6 ቢሊዮን ዩሮ፣ 20.9 ቢሊዮን ደግሞ በብር የሚከፈል ነው፡፡ እስካሁን ለተሠራው ሥራ የተከፈለው 328.9 ሚሊዮን ዩሮና 9.4 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ በውሉ መሠረት 1.3 ቢሊዮን ዩሮና 11.5 ቢሊዮን ብር ቀሪ ክፍያ ይቀራል፡፡ ከዚህ ውስጥም እስካሁን ሥራው ተሠርቶ ክፍያ ያልተፈጸመ 253.8 ሚሊዮን ዩሮ፣ እንዲሁም 149.3 ሚሊዮን ብር ክፍያ ያስፈልጋል፤›› በማለት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገንዘብ ሚኒስቴርን ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኅዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ይህን ቢጠይቅም፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ከአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ለኤሌክትሮና ለኃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች ከሳሊኒ ውጪ አነስተኛ ወለድ በሚከፈልበት ብድር (ኮንሴሽናል ብድር) እንዲካሄድ ወስኖ ነበር፡፡

በዚህ መሠረትም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር) ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ለገንዘብ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር በተገኘ ይሁንታ ኮንሴሽናል ብድር አምጥተው መገንባት የሚችሉ ሰባት ኩባንያዎች ተወዳድረው የቻይና ኩባንያ የሆነው ዳንግ ፋንግ ኢንተርናሽናል አሸናፊ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡

አዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከተሾሙ በኋላም መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለገንዘብ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ፣ ለኃይድሮና ለኤሌክትሮ ሜካኒካል የኮንሴሽናል ብድር እንዲመቻች ጠይቀው ነበር፡፡

‹‹ለኤሌክትሮና ለኃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግዥ የሚያስፈልገው 460.75 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ በውጭ ምንዛሪ የሚያስፈልገው 85 በመቶ ነው፡፡ የእነዚህ ሥራዎች መዘግየት በሲቪል ሥራው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠር ባሻገር፣ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ ላይም መዘግየት እየፈጠረ ስለሆነ ፕሮጀክቱ ለተጨማሪ ወጪና ‹ክሌም› እየዳረገ ነው፤›› በማለት ገንዘብ ሚኒስቴር አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀው ነበር፡፡ 

ነገር ግን ገንዘብ ሚኒስቴር የኮንሴሽናል የብድር አሠራር ተግባራዊ እንዲደረግ ቢወስንም፣ የኃይድሮና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን ለማካሄድ ተወዳድሮ ያሸነፈው የቻይናው ዳንግ ፋንግ ኢንተርናሽናል የኮንሴሽናል አሠራር ብድር እንደሚያመጣ በደብዳቤ ቢገልጽም፣ የኮይሻ ፕሮጀክት ወደ ትክክለኛው የግንባታ ሒደት እስካሁን አለመግባቱ ታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ግን ቀደም ሲል ከተያዘው አቋም የተለየ ሐሳብ ተንቀፀባርቋል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኮይሻ ፕሮጀክት በኮሜርሻል ብድር የተጀመረ ቢሆንም፣ አሁን ብድሩን ማስቀጠል ባለመቻሉ ለተከናወኑ ሥራዎች መንግሥት ፋይናንስ እንዲያመቻችና ፕሮጀክቱም ለተጨማሪ ወጪ እንዳይዳረግ ከዚህ በፊት በተጀመረው ‹ኢንጂነሪንግ ፕሮኪዩርመንት ኮንትራት› (ኢፒሲ) ውል ስምምነት መሠረት እንዲቀጥል ጠይቋል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ባለሙያዎች ግን ይህ አካሄድ አገሪቱን የሚጎዳ እንደሆነ፣ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ኢትዮጵያ ለሚቀጠሉት ዓመታት ከኮሜርሽያል ብድር ርቃ በኮንሴሽናል ብድር የልማት ሥራዎችን እንድታካሂድ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ የሚጥስ በመሆኑ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ይላሉ፡፡ ባለሙያዎቹ ጨምረው እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ጣልቃ ገብተው ጉዳዩን እንዲመለከቱ ያሳስባሉ፡፡ ምክንያቱን ሲገልጹም ፕሮጀክቱ እየተጓተተ ተጨማሪ ወጪ እያስወጣ ከመሆኑም በላይ፣ አገሪቱን ተጨማሪ የብድር ጫና ውስጥ ይካተታል ይላሉ፡፡   

Source: ethiopianreporter 

0
0
0
s2smodern
You are not authorised to post comments.

Comments will undergo moderation before they get published.

Comments powered by CComment

Your Energy Partners in Ethiopia>>>

eepBp tweeter Feed

eepBp Events and Calendars

June 2020
S M T W T F S
1 2 3 4 5 6
7 8 9 10 11 12 13
14 15 16 17 18 19 20
21 22 23 24 25 26 27
28 29 30
Book Your Travel To Ethiopia Here>>>
Afro Experience
+
Afro Experience
+
Historical Tours
+
Natural Wonders
+
Religious and Cultural Festivals
+
Travel Booking

Energy Partners>>>

On Energy

Specialized in integrated sustainable energy solutions in buildings and infrastructure projects.

read more

Green World Technologies

Specilized in marketing of renewable energy technologies in rural areas of Ethiopia.

read more

EWiEN-Ethiopian Women in Energy Network

A women in Energy association that connects and empowers Ethiopian women working in the energy sector

read more

eepBp Active Events

01 May 2020;
08:00AM - 05:00PM
Call for Free Marketing Opportinity for Ethiopia Based Energy Companies:
08 May 2020;
08:00AM - 05:00PM
Call for Publishing Opportunity

Join eepBp Community