የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ሀይል ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይመንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። 100 ሜጋዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ በአዳማ እና አሰላ መካከል የሚገኝ ነው። ይህ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተመጣጣኝ ሀይል ማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል። በተደረሰው ስምምነት መሰረት ሰይሜንስ ጋሜሳ ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ኤስጂ 3 ነጥብ 4 -132 የነፋስ ተርባይኖችን ከፈረንጆቹ 2023 ጀምሮ ያቀርባል ተብሏል።
ሰይሜንስ ጋሜሳ የኢንጅነሪንግ ፣ አስፈላጊ የአገልግሎትና ምርት አቅርቦት እና የሀይል ማመንጫውን የግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ የማስረክብ ሃላፊነት እንዳለበት አፍሪካ ቢዝነዝ ኮሙዩኒቲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ የሀይል ፍላጎቷን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ ከታዳሽ የሀይል ምንጭ ለማሟላት እየሰራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከነፋስ 10 ጊጋዋት ሀይል ማመንጨት አቅም ያላት ሲሆን አሁን ላይ ሀገሪቱ ከነፋስ የምታገኘው ሀይል 324 ሜጋዋት መሆኑ ነው የተነገረው።
Read More: Aligning Ethiopian Energy Markets for Innovation and More Jobs
The Mini-Grid Law Progresses Slowly While Ethiopia Spends Millions for Diesel Power
ለነፋሰ ሀይል ማመንጫው ኢትዮጵያ እና የዴንማርኩ ዳንስኬ ባንክ ግሩፕ የ117 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 94 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮው የባንኩ ግሩፕ በድጋፍ መልክ የሚሰጠው ነው።
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሲሆን 4 ነጥብ 49 ቢሊየን ብሩ ከባንኩ ግሩፕ በተገኘ ድጋፍ እና ብድር የሚሸፈን ይሆናል፡፡
Related
You are not authorised to post comments.
Comments will undergo moderation before they get published.