Ethiopian Energy^Power Business Portal

(thereporterethiopia/ታምሩ ጽጌ, 29 April 2018)

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ (አምባሳደር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ፡፡ አቶ ግርማ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት፣ በቅርቡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙትን ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን (ዶ/ር) ተክተው ነው፡፡

ከሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሠሩ በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) መሰየማቸው ታውቋል፡፡ አቶ ግርማ አምባሳደር ሆነው ወደ አሜሪካ ከመመደባቸው በፊት፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ለ15 ዓመታት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱም የተሻለ እንቅስቃሴ በማድረግ የተለያዩ ለውጦችን ማስመዝገባቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የተቋሙ ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡ እሳቸው ተመልሰው የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑም አዲስ ስለማይሆኑ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

አቶ ግርማ ሰብሳቢ ሆነው በተሰየሙበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ውስጥ፣ ሰሞኑን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ተሾመ ቶጋ (አምባሳደር)፣ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት ወልደሃና (ዶ/ር)፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ አይሻ መሐመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለ መስቀል ተፈራዮሴፍ ረታ (ዶ/ር)  የቦርድ አባል ሆነው ተሰይመዋል፡፡

አቶ ግርማ በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታና በሽግግሩ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

0
0
0
s2smodern

Add comment


Security code
Refresh