October 9, 2026

የአሰላ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

  • May 1, 2020
  • 0

[Spread eepBp if you like it]. 100 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ታስቦ በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ ኢተያ የሚገነባውን የአሰላ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

[Spread eepBp if you like it].

100 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ታስቦ በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ ኢተያ የሚገነባውን የአሰላ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ እንደገለፁት የአሰላ 1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ከተገነቡት የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች መካከል አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ተርባይኖችን በመጠቀም ከፍተኛ ኤነርጂ የሚያመርት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡
 
እንደ አቶ አሸብር ገለፃ በፕሮጀክቱ እያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 45 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው 29 ተርባይኖች ይተከላሉ፡፡
ለንፋስ ኃይል ማመንጫው የሚውለውን ገንዘብ የዴንማርክ መንግስት በስጦታና በብድር እንደሚሸፍን፣ ለ20 ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥና ለአምስት ዓመት የኦፕሬሽንና የጥገና ስራ እንደሚሰራ ስምምነት ላይ መደረሱን ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡
 
ፕሮጀክቱን በተቋራጭነት የዴንማርክና ስፔን ጥምር ኩባንያ የሆነው ሲመንስ ጋሜሳ ሪኒውኤብል ኢነርጂ ሲገነባው የዴንማርኩ ኮዊ ደግሞ በአማካሪነት እንዲሰራ ተመርጧል፡፡
የፊርማ ስነስርዓቱ ተዋዋይ ወገኖች በአካል ሳይገናኙ በቨርቹዋል የተከናወነ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ ከአዲስ አበባ ፤ የዴንማርክና ስፔን ጥምር ኩባንያ የሆነው ሲመንስ ጋሜሳ ሪኒውኤብል ኢነርጂ ደግሞ ከአውሮፓ በመሆን ስካን በተደረገው የስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
 
Visited 1 times, 1 visit(s) today

[Spread eepBp if you like it].
error: Content is protected !!
×