October 9, 2026

(Amharic) ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይሜንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈረመ

  • January 4, 2021
  • 0

[Spread eepBp if you like it]. የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ሀይል ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይመንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። 100 ሜጋዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የአሰላ የነፋስ ሀይል

[Spread eepBp if you like it].

የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ሀይል ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይመንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። 100 ሜጋዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ በአዳማ እና አሰላ መካከል የሚገኝ ነው። ይህ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተመጣጣኝ ሀይል ማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል። በተደረሰው ስምምነት መሰረት ሰይሜንስ ጋሜሳ ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ኤስጂ 3 ነጥብ 4 -132 የነፋስ ተርባይኖችን ከፈረንጆቹ 2023 ጀምሮ ያቀርባል ተብሏል።
 
ሰይሜንስ ጋሜሳ የኢንጅነሪንግ ፣ አስፈላጊ የአገልግሎትና ምርት አቅርቦት እና የሀይል ማመንጫውን የግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ የማስረክብ ሃላፊነት እንዳለበት አፍሪካ ቢዝነዝ ኮሙዩኒቲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ የሀይል ፍላጎቷን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ ከታዳሽ የሀይል ምንጭ ለማሟላት እየሰራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከነፋስ 10 ጊጋዋት ሀይል ማመንጨት አቅም ያላት ሲሆን አሁን ላይ ሀገሪቱ ከነፋስ የምታገኘው ሀይል 324 ሜጋዋት መሆኑ ነው የተነገረው።
 
 
ለነፋሰ ሀይል ማመንጫው ኢትዮጵያ እና የዴንማርኩ ዳንስኬ ባንክ ግሩፕ የ117 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 94 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮው የባንኩ ግሩፕ በድጋፍ መልክ የሚሰጠው ነው።
 
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሲሆን 4 ነጥብ 49 ቢሊየን ብሩ ከባንኩ ግሩፕ በተገኘ ድጋፍ እና ብድር የሚሸፈን ይሆናል፡፡
 
 
 
 
Related
 
 
 
Visited 1 times, 1 visit(s) today

[Spread eepBp if you like it].
error: Content is protected !!
×