October 9, 2026

Ethiopia nears to Power Second Town With Solar Micro-Grid Electric Power Plant

  • November 3, 2020
  • 0

[Spread eepBp if you like it].    Beltu Town is the second town next to Qorile from the 12 rural tons where the Utility is constructing this year.  

[Spread eepBp if you like it].

 
 Beltu Town is the second town next to Qorile from the 12 rural tons where the Utility is constructing this year.
 
ቤልቱ ከተማ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን የነገሃዲ ወረዳ መቀመጫ ነች፡፡ በምስራቁ የሃገራችን ክፍል የምትገኘው ይህች የገጠር ከተማ፤ እስካሁን ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝታ አታውቅም፡፡ ከተማዋ በከንቲባ ደረጃ የምትመራ ቢሆንም ነዋሪቿ በኤሌክትሪክ ዕጦት ምክንያት ማግኘት የሚገባቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገቶች ለዓመታት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
ይህ የሆነው በዋናነት ከተማዋ የምትገኘው ከዋናው የኃይል መስመር /ግሪድ/ ርቃ የምትገኝ በመሆኑ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ለመዘርጋት አስቸጋሪ ስለነበር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤሌቱ ከተማን ጨምሮ ከዋናው የኃይል መስመር /ግሪድ/ ርቀው የሚገኙ መሰል የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኃይል አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ አማራጭ የኃይል ምንጮችን በመጠቀም ተጠቃሚ ለማድረግ ውጥን ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም በመጀመሪያ ዙር 12 የገጠር ከተሞችና መንደሮች በፀሃይ ሃይል አማራጭ ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክት ተነድፎ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በአሁን ወቅት አብዛኞች ወደ መጠናቀቅ የደረሱ ሲሆን፤ በቅርቡ ተመርቆ ሥራ የጀመረው የቆሪሌ የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም ከእነዚህ ውስጥ ይጠቀሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን ነገሃዲ ወረዳ የምትገኘው ቤሌቱ ከተማም በአማራጭ የኃይል ምንጮች ተጠቃሚ ለማድረግ ተቋሙ ከመረጣቸው 12 የገጠር ከተሞችና መንደሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡
 
ለዓመታት በኤሌክትሪክ ዕጦት ምክንያት የተቸገረችው ይህች ከተማ፤ በአሁን ወቅት ችግሯ ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ የፀሃይ ሃይል ማመንጫ እየተገነባላት ይገኛል፡፡
በዚህች ከተማ የሚገነባው የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ በ12ቱ የገጠር ከተሞችና መንደሮች ከሚገነቡት ፕሮጀክቶች ሁሉ ትልቁ ሲሆን፤ 750 ኪ.ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡ ፕሮጀክቱ ኖሪንኮ ኢንተርናሽናል በተሰኘ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ ነው፡፡ እስካሁን እያንዳንዳቸው በፍሬ 22 የሚይዙ 110 ፓኔሎች በድምሩ 2420 ነጠላ የሶላር ፓኔሎች ተተክለውለታል፡፡ የከተማው የማሰራጫ መስመር ዝርጋታ የሚያከናውነው ደግሞ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የባሌ ሮቤ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ነው፡፡
ፕሮጅክቱ ለወረዳው አስተዳደር፣ ለከተማው አስተዳደርና ለነዋሪዎቹ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ሲጠናቀቅም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ደረጃ ያድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እ.ኤ.አ በ2025 ከዋናው የኃይል ቋት 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጮች ደግሞ 35 በመቶ የሚሆነውን ህብረተሰብ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
Visited 1 times, 1 visit(s) today

[Spread eepBp if you like it].
error: Content is protected !!
×