October 9, 2026

Ethiopia Rural Energy Development and Promotion Center-Re-Inauguration Ceremony and Exhibition

  • January 13, 2021
  • 0

[Spread eepBp if you like it].        Source:  Ministry of Water, Irrigation and Energy – Ethiopia/FB   (Walta/FB-Amharic) ኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ

Ethiopia Rural Energy Development and Promotion Center-Re-Inauguration Ceremony and Exhibition
[Spread eepBp if you like it].

 

 

 

 

Source:  Ministry of Water, Irrigation and Energy – Ethiopia/FB

 

(Walta/FB-Amharic)

ኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው::“ከብክለት እና ብክነት የኢነርጂ አጠቃቀም ወደ ዘላቂ የገጠር ኢነርጂ ሽግግር” በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማት እና ማስፋፊያ ማዕከል የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ኢ/ር) በሚቀጥሉት 10 አመታት የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት እና የኢነርጂ አቅርቦት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን የመፍጠር ተልዕኮን ለማሳካት የማዕከሉ መከፈት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ማዕከሉ ለገጠር አካባቢዎች ተስማሚ የሆነ የሀይል ተደራሽነትን ማረጋገጥ ዋነኛ አላማው አድርጎ እንደሚሠራ ተገልጿል። ማዕከሉን ሥራ ከማስጀመር ጎን ለጎን ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ እና ምርትና ቴክኖሎጂ አውደርይ እስከ ጥር 9/2013 ዓ.ም እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።
 
 
 
በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችንና ቴክኖሎጂወችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተናገሩ፡፡  ክቡር ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ዳግም ተደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ በተበሰረበት መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡ 
 
በኢትዮጵያ 80 በመቶ ከሚሆነውና በግብርና ከሚተዳደረው የህብረተሰባችን ክፍል በአብዛኛው የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኝ በመሆኑ ለምግብ ማብሰያና ለመብራት የማገዶ እንጨትን፣ የከብቶች ፍግንና ከከሰልን እንደሚጠቀም ገልጸው ይህን ለመቀየር ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ በማዕከሉ በኩል እንደሚሠራ ሚኒስተሩ ተናግረዋል፡፡ 
 
የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከል በአዋጅ 269/1994 ዓ.ም ተቋቁሞ በገጠር አካባቢ ያለውን የኢነርጂ አቅርቦት እያጠና የኢነርጂ ምንጮችን በማልማትና በማስፋፋት በርካታ ሥራዎችን ሢሠራ ቆይቶ በአዋጅ 691/2003 ማዕከሉ ፈርሶ ስልጣንና ተግባሩ ለውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ለአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን(በወቅቱ ሚኒስቴር ነበር) እና ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተሰጥተው ቆይቶ ነገር ግን በአዋጅ 1097/2011 ዓ.ም እንደገና ተቋቁሞና የመዋቅር ጥናት ተካሂዶ በድጋሚ ተደራጅቶ ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከል የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ የማብሰያ ምድጃዎች፣ የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ፣ የሶላር ሆም ቴክኖሎጂ፣ አነስተኛ ኃይድሮ ፖወርና የባዮ ፊውል ቴክኖሎጂዎች ላይ በስፋት ይሠራል፡፡ 
 
ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘውም በማዕከሉ ወርክሾፕና ላብራቶሪ ቅጽር ግቢ ከጥር 6/2013 እስከ ጥር 8/2013 ዓ.ም የሚቆይ የኢነርጂ ቴክኖሎጆዎችን የሚያሳይ ዓውደ ርዕይም ተዘጋጅቶ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

 

 

Related: 

 

Aligning Ethiopian Energy Markets for Innovation and More Jobs

Tracking SDG 7 Report: The Energy Progress Report 2020- Ethiopia Policy Case Review+ Opinion Piece

The Mini-Grid Law Progresses Slowly While Ethiopia Spends Millions for Diesel Power

 

Visited 1 times, 1 visit(s) today

[Spread eepBp if you like it].
error: Content is protected !!
×